በመጀመሪያው ዙር ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ 2-2 አቻ የተለያየው ዩናይትድ ጨዋታውን ድል አድርጎ ለመውጣት ታቃርቦ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂያቸው አንድሬ ኦናና በሰራቸው ግዙፍ ስህተቶች ሳቢያ በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ውጤት ሳያስጠብቁ ወጥተዋል።
በሜዳ ላይም ከሜዳ ውጪም ውዝግብ ውስጥ የሚገኘው ኦናና ሊዮንን ከገጠሙበት ጨዋታ መልስ አሰልጣኙ ወደ ተጠባባቂ ወንበር በማውረድ ለአልታይ ባይንዲር የመሰለፍ እድል ቢሰጡም በቱርካዊው ስህተቱ ብሶ ታይቷል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ በፕሪምየር ሊግ በኒውካስትል የደረሰባቸው የ 4-1 አሳቃቂ ሽንፈት በቡድኑ ስነ ልቦና ላይ ተጽዕኖ አሳድሮ በምሽቱ ጨዋታ ላይ ጥላ እንዳያጠላ ስጋት አለ።
በእርግጥ ማንችስተር ዩናይትድ በይሮፓ ሊግ መድረኩ የተሻለ የአሸናፊነት ጉዞ ያለው መሆኑ እና የሚጫወተውም በሜዳው እንደመሆኑ ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ የተሻላ ግምት ያሰጥጠዋል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ አንድሬ ኦናና ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ እንደሚመለስ ገልጸዋል። በርካታ ተጫዋቾችን በጉዳት ሳቢያ በቡድን ስብስብ የማያገኙት አሰልጣኙ በማጥቃት አደረጃጀት ላይ የሚረዳቸውን ጆሽዋ ዚርክዜን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ አጥተውታል።
የአጥቂ መስመሩን ሆይሉንድ ፣ ጋርናቾ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሲመሩት፣ በአማካኝ መስመር የካሰሚሮ እና ማውንት ጥምረት ከሊዮን ፈጣን የመስመር ተጫዋቾች አኳያ ለቀያይ ሰይጣኖቹ አስጊ ሆኗል።
በመጀመሪያው 16 ጥሎ ማለፍ ሪያል ሶሶዳድን ባሸነፉበት ጨዋታ ድንቅ የነበረው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ዛሬም ክለቡን እንዲታደግ ይጠበቃል።
ኦሎንፒክ ሊዮን በሊግ 1 ኦንዤን ባማሸነፍ በደረጃ ሰንጠርዥ 4ተኛ ስፍራ ተቀምጦ፣ የአውሮፓ ቻምቲዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማሳካት ተቃርቧል።
በአንጻሩ ማንችስተር የናይትድ በፕሪምየር ሊጉ 14ተኛ ስፍራ እንደመገኘቱ ይሮፓ ሊግን እንደ አቋራጭ መንገድ መጠቀም የግድ ብሎታል። ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ሲል በኦልትራፎርድ ይጀምራል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












