የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፤ ኤምባሲዎችን እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶችን ለመዝጋት ማቀዱን ሲኤንኤን የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰነድ ጠቅሶ አስነብቧል፡፡
ሰነዱ 10 ኤምባሲዎችን እና 17 ቆንስላዎች እንዲዘጉ የሚመክር ሲሆን አብዛኛዎቹ በአውሮፓ እና በአፍሪካ ውስጥ ሲሆኑ የተቀሩት በእስያ እና በካሪቢያን የሚገኙ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
ሰነዱ በኢራቅ እና በሞቃዲሾ ሶማሊያ የዲፕሎማቲክ አባላትን መጠን የመቀነስ ሐሳብም ማቅረቡም ተነግሯል፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ለውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ከሚያወጣው ገንዘብ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋውን ለመቀነስ ማቀዱም ተሰምቷል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከሀገሪቱ ፍላጎት ጋር አይጣጣሙም ያሏቸውን ተቋማት በመዝጋት እና እርዳታዎችን በማቋረጥ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ዘገባው የሲኤንኤን ነው፡፡
በ-ሊያ ክብሮም












