ሺ ይህንን ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በጣለው ታሪፍ ምክንያት የተፈጠረውን መስተጓጎል በመቃወም ነው። በቬትናም ቆይታ ያደረጉት ሺ፣ ከየቬትናም ዋና ፀሀፊ ቶ ላም ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት በአንድ ወገን የሚፈጸሙ ጉልበተኛ አካሄዶችን በጋራ እንዲቃወሙ እና የአለም አቀፍ የነፃ ንግድ ስርዓትን እንደሚደግፉ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የኢንዱስትሪ እና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማረጋጋት መመካከራቸውን እና የጋራ አቋም ይዘዋል፡፡
ሺ ከቬትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚን ቺን ጋር በሃኖይ ባደረጉት ውይይትም፣ ሁለቱ ሀገራት ስልታዊ ግንኙነቶችን እንዲያጠናክሩ እና “የአንድ ወገን ጉልበተኝነትን” በጋራ እንዲቃወሙ አሳስበዋል ሲሉ የቻይና መንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን












