::::::::::::::::::::::::::::::::::
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጠቅላላ ካውንስል የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የስራ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡
በዘጠኝ ወራቱ አፈፃፀም: ከሲቪል ምዝገባ ዘርፍ አኳያ
📌 ከኩነት ምዝገባ እኳያ በጥቅሉ የወቅታዊ ምዝገባ ሽፋን 109.63 በመቶ አፈፃፀም የተመዘገበ ሲሆን የልደት ምዝገባ የፍቺ ምዝገባ እንዲሁም የጉዲፈቻ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን ይህም በከተማው የተዘረጋው የጤና ማዕከላት እና የፍርድ ቤቶች የአንድ ማዕከል የኩነት ምዝገባ አገልግሎት ስርዓት ውጤት መሆኑ ታይቷል።
📌በከተማችን 58,342 ህፃናትን በተወለዱ በ90 ቀናት ውስጥ በወቅቱ የልደት ምዝገባ ለማድረግ ታቅዶ 64,075 ምዝገባ በማድረግ ከ100% በላይ መፈፀም የተቻለ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር 71.15% ብልጫ አሳይቷል።
📌በድምሩ 341,674 ወሳኝ ኩነቶችን ( የልደት፣ ጉዲፈቻ፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ) በወቅቱ፣ በዘገየ እና ጊዜ ገደቡ ባለፈ መዝግቦ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 308,289 በመመዘገብ የእቀዱን 90.23 በመቶ ማከናወን የተቻለ ቢሆንም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1.52% ቅናሽ ያሳይል። ቅናሽ ካሳዩ ምዝገባዎች ጋብቻ ሲሆን ፍቺ በንፅፅር ብልጫ አሳይቷል።
የፍቺ እና ጉዲፈቻ ምዝገባ ከአምናው የምዝገባ ስርዓት ለውጥ የተደረገበት ሲሆን ልክ እንደ ጤና ተቋማት ሁሉ በፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት በመቻሉ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
በአሁኑ ወቅት ጤና ተቋማት ፣ የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በድምሩ 170 ማዕከላት ከመደበኛ ቢሮ ውጭ የወሳኝ ኩነት የአንድ ማዕከል ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከላት ናቸው።
ከነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ አንፃር:
📌 509,938 ነዋሪዎችን ወደ ዲጂታል ምዝገባ ለማስገባት ታቅዶ ክንውን 528,495 (104%) ሲሆን ከአምናው 22.54% ብልጫ አለው፡፡ ይህም በዋናነት በ2016ዓ.ም በማንዋል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 14 ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል በመሸጋገራቸው የመጣ አብላጫ ነው።
📌473, 924 የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በአዲስ ፣ በእድሳት፣ በእርማት እና በምትክ ለመስጠት ታቅዶ 339,048 በመስጠት የእቅዱ 71.54 በመቶ ተከናውኗል። ከዚህም ውስጥ 97.03 በመቶ ዲጅታል መታወቂያ የተሰጣቸው ሲሆን ቀሪው ለአቅመ ደካሞች እና ታማሚዎች የቤት ለቤት አገልግሎት ፣ የጣት አሻራቸው ለተጓዳ እንዲሁም አሻራ መስጠት ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች የተሰጠ ነው።
ተጠያቂነትን በተመለከተ:
📌188 የአሰራር ጥሰት የፈፀሙ፣ አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ የሞከሩ፣ የስራ ቦታ ስነ- ምግረር ያላከበሩ እና በሃሰተኛ መረጃ አገልግሎት ለማግኘት ጥረት ያደረጉ አመራር፣ ፈፃፀሚ እና ባለጉዳይ ተጠያቂ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ከተጠቀሰው ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር 33 መሆኑ ተነግሯል።
በዕለቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክቶሬት አቶ ዮናስ አለማየሁ በጥሩ አፈፃፀም የታዩት እንደተጠበቀ ሆኖ በጉድለቶች ላይ መስራት እንዲቻል የቀጣይ ቀሪ ወራት አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ከተሰጠው አግልግሎት ቁጥር ባሻገር የተገልጋይ እርካታ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስብዋል።
በ- ማህሌት ግርማ












