April 12, 2025

:: :: :: :: :: :: :: :: ::
በተለያዩ የሲዳማ ክልል አከባቢዎች ሲከበር የቆየዉ የፍቼ ጫምባላላ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ከሲዳማ ማህበረሰብ እና ከተለያዩ የከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ፣ የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የፌደራል መንግስት የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሲዳማ ማህበረሰብ አባላትና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












