። ። ። ። ። ። ። ። ።
በአሜሪካ ኒውዮርክ ባጋጠመ የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ 6 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ ።
በኒውዮርክ ሃድሰን ወንዝ ላይ የስፔን ቱሪስቶችን የያዘ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሶስት ህፃናትን ጨምሮ 6 ሰዎች መሞታቸውን የአከባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል አምስቱ ከስፔን የመጡ ቤተሰብ ጎብኚዎች ሲሆኑ ስድስተኛው ሰው አብራሪ መሆኑን የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ኤሪክ አዳምስ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ጎብኚዎችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው ሄሊኮፕተሩ በአየር ላይ ተሰብሮ በማንሃተን እና በኒው ጀርሲ የውሃ ዳርቻ መካከል ባለው ሃድሰን ወንዝ ላይ ተገልብጦ ሲወድቅ የሚያሳይ የምስል ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት አየተዘዋወረ ይገኛል።
ባለስልጣናቱ እንዳሉትም ሄሊኮፕተሩ በኒው ጀርሲ የባህር ዳርቻ ለመንቀሳቀስ በጆርጅ ዋሽንግተን ድልድይ ላይ ከዞረ በኋላ ብዙም ሳይቆይ መቆጣጠሪያውን ሳያጣ እንዳልቀረ ተናግረዋል ።
የአደጋው መንስኤና የሟቾች ማንነት ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ጊዜው አሁን አይደለም ብሏል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












