ይህ ተርሚናል በ3 ነጥብ 9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ለዋናው መንገድ ቅርብ በሆነ ስፍራ ላይ ይገኛልግንባታው ሲጠናቀቅ በሰዓት እስከ 120 አውቶቡሶችን እና 7 ሺህ 200 ተሳፋሪዎችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።
ተርሚናሉ 4 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ ሁለገብ ህንፃን ያካተተ ሲሆን በውስጡም 13 የትኬት መቁረጫ ቢሮዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የስብሰባ አዳራሾች እና የመመገቢያ ስፍራዎች ይኖሩታል።

ከዚህ በተጨማሪም ተሳፋሪዎች ምቹ በሆነ ሁኔታ እንዲጠብቁ ከ1 ሺህ 130 በላይ የማረፊያ ወንበሮች እንዲሁም ከ 8 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የሆነ የአረንጓዴ ስፍራ ተዘጋጅቷል። በተርሚናሉ አጠገብም የታክሲ ተርሚናል እንደሚኖር ተገልጿል።
የህዝብ ትራንስፖርት ስርዓትን ለማዘመን እየተከናወነ ባለው ተግባር ተሳፋሪዎች በጸሀይ እና በዝናብ ሳይንገላቱ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል መናኻሪያዎችን ለማዘመን በሚሰራው ስራ የአቃቂ መናኻሪያ የኤሌክትሮኒክስ የትኬት መቁረጫ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ለሌሎች ሞዴል በሚሆን ደረጃ የተገነባ መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል::












