:::::::::::::::::::::::::::::
የ32ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ነገ ቀን 8፡30 ማንችስተር ሲቲ በሜዳው ክሪስታል ፓላስን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጀመራል።
ውሃ ሰማያዎዎቹ የቻምፒዮንስ ሊግ ስፍራን የዘው ለማጣናቀቅ ፉክክር ውስጥ ይገኛሉ።አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው 11ኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ፓላስ፣ በወቅታዊ አቋሙ ጠንካራ ነው። በሊጉ ካደረጓቸው ካለፉት 5 ጨዋታዎች በ1 ዱ ብቻ ነጥብ ሲጥሉ ቀሪዎቹን አሸንፈዋል።
6ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ሲቲ ባሳለፍነው ሳምንት በማንቹሪያን ደርቢ ነጥብ ጥሏል፣ በነገው ጨዋታ አሸናፊ መሆን ከቻለ በጊዜያዊነት 4ተኛ ስፍራን ይቆናጠጣል።
የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ሻምፒዮኑን የለየ የሚመስለው ፕሪምየር ሊጉ፣ ከ3ተኛ እስከ 11 ደረጃ በተቀመጡ ክለቦች መካከል ያለው የነጥብ መቀራረብ ጨዋታዎች በተደረጉ ቁጥር መፋለስ ይታይበታል።ፓላስ ቀሪ ጨዋታ እያለው ከሲቲ የሚያንሰው በ9 ነጥቦች ነው።
በማንችስተር ሲቲ በኩል የተሰማ አዲስ ጉዳት የለም። በደርቢው ጨዋታ ከተጠባባቂ ወንበር የተነሱት ጀረሚ ዶኩ እና ፊል ፎደን ወደ ቋሚ አሰላለፍ ይመለሳሉ ተብሏል።
መልሶ ግንባታ ላይ የሚገኙት ሲቲዎች ክሪስታል ፓላስ ላይ የውጤት የበላይነት ቢኖራቸውም፣ የለንደኑ ቡድን አይረሴ ድሎችን ኤቲሃድ ላይ አስመዝግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












