፡፡ ፡፡ ፡፡ ። ። ። ። ። ።
አሜሪካና ሩሲያ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አማካኝነት የእስረኛ ልውውጥ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡
የሩሲያ ፌደራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) የአሜሪካ ዜግነት ያላት ከሲና ካርሊናን በሩሲያው አርተር ፔትሮቭ መለዋወጣቸውን ገልጿል፡፡
ሩሲያ፤ ከአሜሪካ ጋር የተደረገውን የእስረኛ ልውውጥ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላባረከተችው አረብ ኤምሬትስ ምስጋናዋን አቅርባለች ተብሏል፡፡

የሩሲያ ዜግነት ያለው ፔትሮቭ በፈረንጆቹ 2023 በግሪክ ሳይፐረስ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ነበር ወደ አሜሪካ በ2024 ተላልፎ የተሰጠው፡፡
ፔትሮቭ የተከሰሰው የተከለከሉ እቃዎችን በህገ ወጥ መንገድ (Export Control Act) በመጣስ ሲያዛዋውር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
ፔትሮቭ እስከ 20 ዓመት እስር እንደሚጠብቀው ተገለጾ የነበረ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት ስምምነት መፈታቱ ነው የተነገረው ፡፡
በሌላ በኩል ከሲና ካርሊና የአሜሪካና ሩሲያ ጥምር ዜግነት ያላት እንዲሁም የሎስ አንጀለስ ነዋሪ ስትሆን፣ በፈረንጆቹ 2024 በሩሲያ የካትሪንበርግ ከተማ ለዩክሬን ስትሰልል በቁጥጥር ስር መዋሏ ተመላክቷል፡፡
አናዶሉ ፣ አልጀዚራ ዘግበውታል ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












