::::::::::::::::::::::::::
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ከግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ የበረራ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።
ይህ አዲስ የበረራ አገልግሎት በሳምንት አራት ቀናት የሚደረግ መሆኑንም አየር መንገዱ አስተውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጀምረው አዲስ የበረራ መስመር መንገደኞች በተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ የደማቅ ባህል እና ሰፊ ኢኮኖሚያዊ እድሎች ባለቤት ወደ ሆነችው ሻርጃ ከተማ በቀላሉ እንዲጓዙ እንደሚስችልም አስታውቋል።












