ቭ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በሊጉ 3ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ በወራጅ ቀጠና 17ተኛ ላይ የሚገኘውን ስሑል ሽረን ይገጥማል።
ባህርዳር ከመሪው ኢትዮጵያ መድን የ11 ነጥብ ልዩነት ያለው ሲሆን በጨዋታው አሸናፊ መሆን ከቻለ ነጥቡን ሁለተኛ ስፍራ ከሚገኘው ወላይታ ዲቻ ያስተካክለል።
በአንጻሩ ስሑል ሽረ ከወራጅ ስጋት ለመላቀቅ በቀሪ ጨዋታዎች ማሸነፍ ይኖርበታል።ምሽት 12 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከ ከመቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። 4ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ቡና ከመቻል የ4 ነጥብ ልዩነት አለው።
ቡድኖቹ በጨዋታው የሚያገኙት ነጥብ የደረጃ ለውጥን የሚያስገኝ በመሆኑ ከፍተኛ ፉክክር የደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። ጨዋታዎቹ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚደረጉ ይሆናል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












