።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ፕሬዚዳንት ሃሪ ቱርማን አሜሪካ ለአውሮፓ ሃገራት የኢኮኖሚ ማገገሚያ እቅድ “የማርሻል ፕላንን” የፈረሙት ከ 77 አመት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት እ.አ.አ በ1948 ነበር።
ለመሆኑ ማርሻል ፕላን ምንድነው ?
የሁለተኛው የአለም ጦርነት መላው አውሮፓን በውጊያው ተሳታፊ ያልሆኑ አገራትን ጭምር በከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ከትቶ ያለፈ ጠባሳ ነው።
በጦርነቱ 11ኛው ሰዓት ላይ ተሳታፊ የነበረችው አሜሪካ ከየትኛውም አገር በተሻለ የኢኮኖሚ መረጋጋት የሰፈነባት፣አጋጣሚውም ልዕለ ሃያል ያደረጋት ነበረች።
ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ አለም በሶሻሊስት እና ካፒታሊስት ጎራ ሲከፈል አሜሪካ ከወጠነቻቸው እቅዶች አንዱ የንግድ ትስስርን በመፍጠር ለካፒታሊስት ካምፕ አጋሮችን ማበጀት ነበር።
ከዚህም ውስጥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆርጅ ማርሻል ሃሳብ አመንጪነት የቀረበው “በጦርነት የደቀቁ የአውሮፓ አገራትን ኢኮኖሚ ማነቃቃት” የሚለው እቅድ ይገኝበታል።
በሃሳቡ ባለቤት ስም የተሰየመው “ማርሻል ፕላን” አላማው በጦርነት የወደሙ የልማት አውታሮችን መልሶ መገንባት፣ ኢኮኖሚን ማነቃቃት እና ለዘለቄታው የአሜሪካ – አውሮፓ የንግድ ትስስር መፍጠር እና በዋናነት የሶቪየት ሕብረትን ኮምዩኒዝም መግታት ነበር።
በእቅዱ አሜሪካ 13.3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ስታደርግ፣16 የአውሮፓ አገራትም ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
ጆርጅ ማርሻል ያቀረበው እቅድ ከተጠበቀው በላይ ውጤታማ መሆኑ የኖቤል የሰላም ሽልማት ሲያስገኝለት፣አገሩ አሜሪካም በአውሮፓ አገራት ያላትን ተሰሚነት ገንብቶላታል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












