።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ከ ኤቨርተን የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።
ፕሪምየር ሊጉን ትላንት አርሰናል እስኪያሸንፍ በ12 ነጥብ ልዩነት በመምራት ላይ የነበረው ሊቨርፑል የነጥብ ልዩነቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ይጫወታል።
ቀዮቹ ከአለማቀፍ የውድድር ጨዋታዎች በፊት በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች በካራባኦ ካፕ ፍጻሜ በኒውካስትል ዋንጫውን ሲቀሙ ከቻምፒዮንስ ሊግም በፒኤስጂ ከውድድሩ ውጪ ተደርገዋል።
ከምሽቱ ጨዋታ አስቀድሞ አሰልጣኝ አርን ስሎት በሰጡት መግለጫ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኮነር ብራድሊ ከጉዳቱ አገግሞ ለጨዋታው በቡድን ስብስቡ መካተቱን ተናግረዋል።
በክረምት ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል የተስማማው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በቁርጭምጭሚት ጉዳት በምሽቱ ጨዋታ አይኖርም።
ከአሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ዳግም መመለስ በኋላ የውጤት መነቃቃት ላይ የሚገኘው ኤቨርተን ምንም እንኳን በቀደመ ግንኙነታቸው በሜዳው ነጥብ ማስጣል ቢችልም በአንፊልድ ሊቨርፑልን ለማቆም ይቸግረዋል ተብሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












