ሰሚ አውቶሜትድ ኦፍሳይድ ቴክኖሎጂ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የፊታችን ቅዳሜ ማንችስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ በሚያደርጉት ጨዋታ ለመጀመርያ ጊዜ የሚተገበርበት እንደሆነም ተገልጿል።
ቀደም ብሎ መተግበር የጀመረውን በምስል የታገዘ ዳኝነት ወይም ቫርን ለማገዝ ስራ ላይ የሚውለው ሰሚ አውቶሜትድ ኦፍሳይድ ቴክኖሎጂ ከጨዋታ ውጭ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን በተመለከ የሚተላለፉ ውሳኔዎች ወጥነት እንዲኖራቸው ከማድረጉ በተጨማሪ የሚባክነውን ሰዓት ለመቀነስ የሚያግዝ ይሆናል ተብሏል።
የኳታር ዓለም ዋንጫን ጨምሮ የስፔን ላሊጋ እና የጣልያን ሴሪ ኤ እንዲሁም የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ሰሚ አውቶሜትድ ኦፍሳይድ ክኖሎጂው ቀደም ብሎ መተግበር የጀመረባቸው ናቸው።
በፕሪምየር ሊግ በተለያዩ ጨዋታዎች በቫር እገዛም ጭምር የሚታዩ ውዝግቦችን ያስቀራል ተብሎለታል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












