፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
9ኛው ሆርቲፍሎራ ኤክስፖ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ።
ኤክስፖ ኢትዮጵያ በአለምአቀፍ ንግድ ውስጥ በይበልጥ ተሳታፊ እንድትሆን የሚያደርግ ነው የተባለ ሲሆን አዳዲስ የኢንቨስትመንት በሮችን የሚከፍት ነው ተብሏል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ አምራቾች ላኪዎች እና አስመጪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ለሀገራችን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ የሚገኘውን የሆልቲካልቸር ዘርፍ ለማዘመን የሚረዱ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ይተዋወቁበታል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ባላት የተፈጥሮ አቅም ልክ ለምግብነት የሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ለውጪ ገበያ እያቀረበች አይደለም ያሉት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጤናማ የስራ ስፍራ ለመፍጠር እና ዘርፋን ለመደገፍ ጠንክሮ አየሰራ ነው ብለዋል።

አክለውም በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሆርቲካልቸር ዘርፍ ያሉ እንደሎችን መጠቀም እንደሚገባ በመጠቆም፤ መንግስት ዘርፉ የሚያስፈልገውን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ለመፍታት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
ሆርቲካልቸር በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በሕግ ማዕቀፍ ክፍተት፤ በመሬት አቅርቦትና በሰላም እጦት ቢፈተንም ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ዘርፍ ነው፡፡

በተያዘው በጀት አመት ኢትዮጵያ ከአበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ በተያዘው በጀት አመት ስምንት ወር ውስጥ 366 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተነግሯል።
በ-ሰብለ ወንድማገኝ












