::::::::::::::::::::::::::::
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለመፍታት ፍቃደኛ እንደሚሆኑ ተስፋቸውን ገለጹ፡፡
ትራምፕ ፤ ዩክሬን ከአሜሪካ ጋር የማዕድን ስምምነት ለማድረግ የጀመረችውን እንቅስቃሴ አንዳታቋርጥ ማስጠንቀቂያም ሰጥተዋል፡፡

የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን በሰላም ለመጨረስ ብዙ ርቀት መሄዳቸውን የሚናገሩት ትራምፕ ፤ ጦርነቱን ለመቋጨት ሩሲያ ትልቅ የቤት ስራ እንዳለባትም ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ ይህን የምታደርግ ከሆነ በዘይት ምርቷ ላይ ታሪፍ እንደሚጥሉ ገልጸው ዘለንስኪም ለዚህ ድርድር ፍቃደኛ እንደሚሆኑ አምናለሁ ብለዋል ትራምፕ ፡፡
ትራምፕ፤ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ ኬይቭ ከዋሽንግተን የወሰደችውን እርዳታ መመለስ አለባት ቢሉም፤ ዘለንስኪ ከዋሽንግተን የወሰድኩት ምንም ነገር የለም ሲሉ ትራምፕን ተቃውመዋል ፡፡ ዘገባው የአር ቲ ኒውስ ነው፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












