፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ዘንድሮ ለ 23ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ በተለያዩ መርሀ ግብሮች እንደሚካሄድ ተገለፀ።
ጤና ሚኒስቴር ከኒያ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚካሄደውን የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በተለያዩ ፕሮግራሞች ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።
የ 2017 ዓ.ም ሀገር ዓቀፍ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ የጤና ሚኒስቴር በኦቲዝም ዙሪያ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ወሩን አስመልክቶ እስካሁን በኢትዮጵያ ባሉ 8 ክልሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራታቸዉ የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በአዕምሮ እድገት ዉስንነት ላይ ልትሰራ የሚገባትን ስራ መስራት እንድትችል መንገድ የሚከፍት እንደሆነ ተጠቁሟል።
በኦቲዝም ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች በበኩላቸዉ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠዉ ጠይቀዉ ሁሉም ማህበረሰብ ሀላፊነት ስላለበት በርብርብ ሊሰራ ይገባል ሲሉ በመግለጫዉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
በ- ሊያ ክብሮም












