።።።።።።።።።።።።።።።
“ከጥንት ጀምሮ እስካሁን የዘለቀው የአሜሪካና የካናዳ ግንኙነት አሁን ተቋጭቷል!”ሲሉ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ ተናገሩ።
የሊበራል ፓርቲው መሪ በኢኮኖሚ ፣በደህንነት እና በወታደራዊ ስርአት ከጥንት እስከዛሬ የዘለቀዉ ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ግንኙነት ማብቃቱን ከካቢኔ ስብሰባ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የዶናልድ ትራምፕ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ላይ በትላንትናው እለት ያሳለፉትን የ25 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ተከትሎ ነው።
ካናዳና አሜሪካ ከፈረንጆቹ 1965 አንስቶ በተሽከርካሪዎች ዙሪያ ያሰሩት ውል እንደነበር አስታውሰው ፤ አሁን ግን በታሪፍ ጭማሪው ምክንያት አብቅቷል ብለዋል።
ከዚህ በኋላ ካናዳውያን እራሳቸው የሚቆጣጠሩት ኢኮኖሚ መገንባት አለባቸው፤ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲሁ ማጤን ይገባል ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ወር ከካናዳ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የአልሙናይ እና ብረታብረት እንዲሁም ሌሎች ምርቶች ላይ የ25 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ማድረጋቸው ይታወሳል፤
አሁን ላይ ደግሞ ካናዳን ጨምሮ ከአውሮፓ የሚገቡ ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ላይ ሌላ የ25 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ አፅድቀዋል።
ጭማሪው ከመጪው ሚያዝያ 2 አንስቶ ተግባራዊ ይደረጋል።
የአውሮፓ ህብረት የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጉዳት ከካናዳ ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቆመ ሌላ የታሪፍ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












