::::::::::::::::::::::::::::::::::
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የ1446ኛው የኢድ አል ፊጥር በዓልን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ጨረቃ ቅዳሜ ከታየች በዓሉ እሁድ እንደሚውል የገለፀ ሲሆን ካልሆነ ግን በዓሉ ሰኞ ዕለት እንደሚውል ጠቁሟል።
ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ውስጥ ሲያከናውናቸው የቆየውን መልካም ተግባራት በሌሎች ወራትም ይዞ ሊቀጥል ይገባዋል ብሏል።

የኢድ ሰላቱ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚሰገድ የተገለፀ ሲሆን ድምፁን ተደራሽ ለማድረግ በሶስት ኤፍ ኤም ጣቢያዎች በቀጥታ እንደሚተላለፍ አስታውቋል።
እለቱ የደስታ በመሆኑ ደስታውን ሊያደፈርስ የሚችል ማንኛውም ተግባር ማከናወን እንደማይፈቀድ የገለፀው ከፍተኛ ም/ቤቱ የመሰረተ ልማቶች መጠበቅ እንደሚገባም አሳስቧል።
ከኢድ ሰላቱ አስቀድሞ ዘካተል ፊጥርን በማውጣት ኢስላማዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጠይቋል።
በ -አክረም ኑርያ











