የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ተቋም ማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የማስተር ካርድ ክፍያ ሥርዓትን አስጀምሯል።

ማስተር ካርዱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ እና የማስተር ካርድ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ማርክ ኢሊዮት በጋራ አስጀምረዋል።
ባንኩ ያስጀመረው የማስተር ካርድ ክፍያ ሥርዓት በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ለማሻሻል የሚያግዝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱ ዓለም አቀፋዊ ግብይቶችን ለመፈፀም የሚያስችል ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም ከማስተር ካርድ ጋር በፋይናንስ ዘርፍ በትብብር ሲሰራ መቆየቱም ተገልጿል።
በ-ሀሴት ኃይሉ












