።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሊዮኔል ስካሎኒን ቡድን ጎሎች ጁሊያን አልቫሬዝ ፣ ኤንዞ ፈርናንዴዝ ፣ አሌክሲስ ማክ አሊስተርና ጁሊያኖ ሲሞኒ አስቆጥረዋል።
ቡድኑ ያለ ሊዮኔል ሜሲና ላውታሮ ማርቲኔዝ ተጫውቶ ነው ታሪካዊ ተቀንቃኙን ብራዚል በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፈው።
የዶሪቫል ጁኒየር ብራዚልን ብቸኛ ጎል የዎልቭሱ አጥቂ ማቲውስ ኩኛ በ26ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
ብራዚል ከዚህም በላይ ጎሎች ተቆርጥረውባት ባለመሸነፏ ዕድለኛ ናት የሚያስብል ምሽትን አሳልፋለች።
ቡድኑ በግጥሚያው በሁሉም መመዘኛዎች ብልጫ የተወሰደበት ሲሆን ኢላማቸውን የጠበቁም ያልጠበቁም 2 ሙከራዎችን ብቻ አድርጓል።
ባለሜዳዋ አርጀንቲና በአንጻሩ 7 ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን አድርጋ ነው 4ቱን ወደ ግብነት የቀየረችው።
ብራዚል ሃሙስ ዕለት ኮሎምቢያን በሜዳዋ 2-1 ካሸነፈች በኋላ ለሌላ የከፍታ ጉዞ ያደረገችው ወሳኝ ግጥሚያ ነበር።
የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ “ይህ የቡድን ድል ነው፣ በቡድን ተጫውተናል፣ ለዚህም ነው ብራዚልን ማሸነፍ የቻልነው” ብለዋል።
ቀደም ብሎ ማክሰኞ ዕለት ኡራጓይ እና ቦሊቪያ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ከተለያዩ በኋላ አርጀንቲና በ2026 የዓለም ዋንጫ ታሳታፊነቷን ያረጋገጠች የመጀመሪያው የደቡብ አሜሪካ ሀገር መሆኗ ይታወሳል።
ብራዚል በአንጻሩ ከ14 ጨዋታዎች 21 ነጥብ በመሰብሰብ ከአርጀንቲና፣ ኢኳዶርና ኡራጓይ በመቀጠል በደረጃ ሰንጠረዡ 4ኛ ላይ ተቀምጣለች።
ከደቡብ አሜሪካ ኮንፌዴሬሽን ከፍተኛ 6 ሀገራት በቀጥታ ወደ ዓለም ዋንጫው እንደሚያልፉ ይታወቃል።
7ኛው ቡድን በ6ቱ ኮንፌዴሬሽኖች መካከል በሚካሄደው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ይሳተፋል።
በ-ይበልጣል ሰውነት












