።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ማቴታ ከ3 ሳምንታት በፊት በሜዳቸው ሚልዎልን 3-1 ባሸነፉበት የኤፍ ኤ ዋንጫ የ5ኛ ዙር ጨዋታ የሚልዎል ግብ ጠባቂ ሊያም ሮበርት በፈጸመበት ከባድ ጥፋት ለህክምና በአምቡላንስ መወሰዱ አይዘነጋም።
ፈረንሳዊው አጥቂ የግራ ጆሮው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ገጥሞት የቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። ግዙፉ አጥቂ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ሊርቅ ይችላል ተብሎ የተነገረ ቢሆንም 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ ልምምድ ተመልሷል።
ማቴታ ክሪስታል ፓላስና ፉልሃም የፊታችን ቅዳሜ በሚያደርጉት የኤፍ ኤ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ጆሮው ላይ መከላከያ ማስክ አድርጎ ይሰለፋል ተብሏል።
የ27 ዓመቱ ፈረንሳዊ አጥቂ በያዝነው የውድድር ዘመን ለክለቡ 12 ግቦችን አስቆጥሯል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ