።።።።።።።።።።።።።።።።።
ህንድ እና የአፍሪካ መንግስታት የባህር ሀይል ልምምድ ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ፡፡
ልምምዱ በወደብና ባህር ላይ እንደሚሆንም የህንድ ባህር ሀይል ገልጿል፡፡
በህንድና አስር የአፍሪካ ሀገራት መካከል የባህር ላይ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው የተባለው ልምምድ በህንድ ውቅኖስ ላይ እንደሚደረግም ተመላክቷል፡፡
በሳንስክሪት ቋንቃ አኪሚ ወይም አንድነት (AIKEYME – unity) የተባለው የጋራ የባህር ላይ ልምምድ ታንዛኒያ ፣ ኮሞሮስ ፣ ጅቡቲ ፣ ኤርትራ ፣ ኬንያ ፣ ማዳካስካር ፣ ሞሪሺየስ ፣ ሞዛምቢክ ፣ ሲሼልስ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል ተብሏል፡፡
አር .ቲ. ኢንተርናሽናል ዘግቦታል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን