፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሶማሌና የአፋር ክልሎች ህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የመድረኩ ቅድመ ምክክር ከክልሎቹ የተውጣጡ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል።
የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በዚሁ ወቅት፥ የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች የጋራ ታሪክ እንዳላቸው አውስተው፤ በጋራ የመልማት፣ የማደግና የመበልጸግ አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና የጋራ ልማትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ የሚካሄደው የወንድማማችነት መድረክ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ መፍትሔ በመስጠት መግባባትንና የጋራ ልማትን ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የክልሎቹ መንግሥታት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የወሰዱት ቁርጠኝነት ለህዝቡ ትልቅ እፎይታን የሰጠ መሆኑን የቅድመ ምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
ውይይቱ የአፋርና ሶማሌ ክልል ህዝቦችን ግንኙነት በማጠናከር ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ጉልህ ፋይዳ እንዳለውም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡












