።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ፖለቲካው ዓለም እመለሳለሁ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ባይደን ለደሞክራት ፓርቲ ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ለመጀመር ማሰባቸውን የአሜሪካው NBC News ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ማረጋገጡን ጠቅሶ የሩሲያው አር ቲ ኒውስ አስነብቧል፡፡
ባይደን ወደ ፖለቲካው እንዲመለሱ ገፊ ምክንያት ከሆናቸው አንዱ ዲሞክራቶች በህዝብ ዘንድ ያላቸው ቅቡልነት እየቀነሳ መምጣቱን ተከትሎ ነው ሲሉ ከአዲሱ የዲሞክራት ብሄራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኬን ማርቲን ጋር በነበራቸው ቆይታ መናገራቸው ታውቋል፡፡
ምን እንኳ ባይደን ወደ ፖለቲካው ዓለም ተመልሼ ፓርቲየን እታደጋለሁ ቢሉም ከእድሜያቸው መግፋት አንጻር እንደማይሳካላቸው የፖለቲካ ተንታኞች አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛል ፡፡
ዘ ፕረስ ዩናይትድ ፤ አር ቲ እና ስፑትኒክ ዘግበውታል ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












