የክልሉ የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ እስማኤል ዩሱፍ የተቋሙ የስድስት ወራት አፈጻጸም በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ እስማኤል በበጀት ዓመቱ ለዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ለመፍጠር ከታቀደው 5 ሺህ 034 የስራ እድል ውስጥ ለ 4 ሺህ 822 ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉንና አፈጻጸሙም 95 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህም ውስጥ በከተማ ለሚገኙ 2 ሺህ 556 የስራ ዕድል እንዲሁም 1 ሺህ 842 በገጠር ወረዳ ለሚገኙ ወጣቶች ስሆን 424 የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት የተፈጠረላቸው ዜጎች መሆኑን አስረድተዋል።
የስራ ዘርፎቹም በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች መሆኑንም ነው የገለፁት።
ባለፉት ስድስት ወራት ለኢንተርፕራይዞች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸዋል።
በስድስት ወራት ግዜ ውስጥ ለኢንተርፕራይዞች የማምረቻና የመሸጫ ስፍራዎችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር 25 ሼዶችን ለኢንተርፕራይዞች መሰጠቱን ጠቁመዋል።
በክልሉ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 41 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል።
የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሽፋንን ለማሳደግ 1 ሺህ 611 ለሚሆኑ ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በኦንላይን (online) የተደገፈ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ገልጸው ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብን ገልጸዋል።
የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሚያስችሉ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ የማጠናከር ስራዎችን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
የሕዝቡን ችግር በማባባስ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚሯሯጡ ነጋዴዎች ላይ አስተማሪ የሆነ ህጋዊ ዕርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የህዝቡን የኑሮ ውድነት ለማቃለል በተለይም መሰረታዊ የሆኑ ፍጆታዎችን የማቅረብ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የጥሬና የፋብሪካ ውጤቶች የግብዓት አቅርቦትን ለማሻሻል በ6 ወር ውስጥ 287 ቶን በላይ ግብዓት ለማቅረብ መቻሉንም እንዲሁ።
ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሊዝ ፋይናንስ አቅርቦትን ወደ 12 ሚሊዮን 879 ሺህ 864 ብር ለማሳደግ ታቅዶ ብር 30 ሚሊዮን 300 ሺህ ብር መቅረቡን አመልክተዋል። በቀጣይ ሰፋፊ የስራ እድልን ለመፍጠርና የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት ስራ በከፍተኛ ትኩረት ይሰራልም ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።












