ከተጎጂዎቹ መካከል ሁለቱ በድንጋጤ ከህንጻው ላይ ዘለው ከወጡ በኋላ ህይወታቸው ማለፉን የሆቴሉ ባለቤት ገልፀው በሆቴሉ 234 እንግዶች እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡
የሆቴሉ ውጫዊ ክፍል በእንጨት መሰራቱ የእሳቱን ስርጭት እንዲፋጠን እንዳደረገው የሆቴሉ ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡ መንግስት በአደጋው ላይ ምርመራ እንዲያደርጉ ስድስት አቃቤ ህጎችን መሾሙን የሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ኤን ቲቪ ገልጿል፡፡
ሆቴሉ ከኢስታንቡል በስተምስራቅ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በኮሮግሉ ተራሮች ውስጥ የሚገኝ ታዋቂ ሪዞርት ነው ሲል የዘገበው ኒውስ ደይ ነው።
በ-ሊያ ክብሮም












