፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 25 2017| NBC ETHIOPIA- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቻይናዋ ጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ሹ ኩንሊን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከቻይናዋ ጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ሹ ኩንሊን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አስፍረዋል።

ሚስተር ሹ ኩንሊን በህዳር ወር በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የጂያንግሱ ግዛትን እንድንጎበኝ ባቀረቡልን ግብዣ መሰረት በግዛቱ ጉብኝት በማድረግ ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ በጉብኝታችን ወቅት ከጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ እና አመራሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በመወያየት በቀጣይ በጥቅሉ በኢንቨስትመንት ፣ በንግድ ፣ በቱሪዝም ፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፎች ላይ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በቀጣይም በትብብር ለመስራት ተግባብተናል ነው ያሉት፡፡

ሚስተር ሹ ኩንሊን በጂያንግሱ ግዛት በነበረን ጉብኝት ላደረጉልን መስተንግዶ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ ብለዋል።












