፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 24 2017| NBC ETHIOPIA- ጤና ሚኒስቴር ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለወሊድ እና ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የሚውሉ 370 አምቡላንሶችን አስረከበ።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ዛሬ ማለዳ ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮቹ የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ማስረከባቸውን የገለፀው ኢዜአ ነው።
አምቡላንሶቹ በጤናው ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችንን ለማሳካት ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ከ3 ሺህ በላይ አምቡላንሶች ለከተማ አስተዳደሮችና ለክልሎች እንዲተላለፉ መደረጉንም አስታውሰዋል።
በዚህም በተለይ በእናቶች ሞት እና በድንገተኛ አደጋ ቅነሳ ዙሪያ አመርቂ ውጤት እንደተመዘገበበት ነው ያነሱት።












