፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 24 2017| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በቂ የምርት አቅርቦት ለገበያ ዋጋ መረጋጋት በሚል መሪ ቃል የእዉቅና መድረክ አዘጋጅቷል። የቅዳሜ እና የእሁድ ገበያዎች ለህብረተሰቡ በስፋት ተደራሽ እንዲሆኑና በአነስተኛ ዋጋ ለሕብረተሰቡ እንዲቀርቡ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነም በመድረኩ ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ መድረኩ የኑሮ ዉድነትን ለማቃለልና አምራችና ሸማቹን በቀጥታ ለማገናኘት በስፋት እንደሚሰራ ጠቁሟል። አሁን ላይ በአዲስአበባ ከተማ ብቻ በ11 ክፍለከተማ የእሁድ ገበያ ተግባራዊ ሆኗል። ወደ 10 የሚሆኑ የገበያ ማዕከላትም መገንባት ችለዋል።

በ119 ወረዳ ከ197 በላይ የአምራች አቅራቢዎች መሳተፍ የቻሉ ሲሆን 126 ሸማች ማህበሮች እና 282 ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ መሆን ችለዋል።

በማስቀጠልም የገና ዋዜማን አስመልክቶ ምንም አይነት የምርት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ስራዎችን እንደተሰሩ ተመላክቷል። ይህን ዓላማ እዉን እንዲሆን ላደረጉ ከተለያዩ ክፍለከተማ እና ወረዳዎች ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት የእዉቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በቀጣይም የግብይት ስርአቱ የተሳካ እና ዘመናዊ እንዲሆን ለማስቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ከተለያዮ አቅራቢ አካላት ጋር የፊርማ ስነስርዓት አከናዉነዋል።
በ-ማህሌት ግርማ












