፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ |ታህሳስ 24 2017| NBC ETHIOPIA-“ንባብ ለሰላም ግንባታ!”በሚል መሪ ቃል 10ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቫል በአዲስ አበባ ሙዚየም ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሰው በመድረኩ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ንባብ ለሰላም ግንባታ መሰረት ነው ብለዋል።

ልዩነት ስጋት ሳይሆን የእውቀትና የውበት ምንጭ መሆኑን ገላጭ ነው ተብሏል።ትውልድና ሀገርን መገንባት የሚቻለው አንባቢ ትውልድ ሲኖር ነው ለዚህም ከአብርሆት ቤተ መፅሀፍት አንስቶ በሁሉም ክ/ከ መፅሀፍት ቤቶች እንዲገነቡ መደረጉም በመድረኩ ተነስቷል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ፌስቲቫል የመፅሀፍት ኤግዚቢሽንና ባዛር ፣ የተማሪዎች የንባብ ውድድርና ሌሎችም መርሀግብሮች እንደሚኖሩ ተነስቷል።
የ-አብስራ ሚሊዮን












