፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 16 2017| NBC ETHIOPIA- ሰላም እና መረጋጋትን ለማምጣት ዋና ግቡ አድረጎ እየሰራ የሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) እና የአመራር ልማት ተግባሩን ለማስፋት በሚሰራው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ መካከል ነው ስምምነቱ ተፈረመው።
በኢትዮጵያ የኢጋድ ተጠሪ አበባው ቢሆነኝ ኢጋድ በቀጠናው ሰላም ለማስፈን፣ በጤና፣በማህበራዊ አገልግሎት ፣በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና በአመራር ላይ የሚሰራውን ስራን በማንሳት የጋራ ስምምነቱ የአመራር እቅም ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው የአመራርን አቅም ለማሳደግ ከተለያዪ ሀገራት ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑ በመጠቆም፣ የተደረገው ስምምነት በኢጋድና አባል ሀገራቱ ትስስር የሚፈጥር ነው ብለዋል።
በቀጠናው ሰላም ለማስጠብቅ፤ ሀገራቱን ከማስተሳስር አኳያ የሚሰራው ስራ አስተሳስሮ ለመስራት ስምምነቱ ያግዛል ተብሏል።
በ-ሰላም ይልማ












