፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 02 2017| NBC ETHIOPIA- የኬንያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ አመራሮችና የኮሌጁ ሰልጣኞች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን የአየር መንገዱን መሠረተ ልማት በማስፋፋትና የዘርፉን ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ በማዋል አገልግሎቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በተሰራው ስራ ውጤታማ ሆነናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ለማስተሳሰርና ከዓለም ጋር ለማገናኘት እየሰራ እንደሆነም ገልፀዋል።

የልካን ቡድኑ አባላት በነበራቸው ጉብኝት ጠቃሚ ተሞክሮ ማግኘታቸውን ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።











