Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

16ቱ ብርቱካናማ ቀናት ከሕዳር 16 – ታህሳስ 1 ድረስ ፆታዊ ጥቃትን ለማውገዝ የሚደረግ አለማቀፋዊ ንቅናቄ

November 28, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ህዳር 19 2017| NBC ETHIOPIA -አለም አቀፍ የጸረ- ጾታዊ ጥቃት ቀናት  ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ “UNITE to End Violence against women and Girls”፤ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ “የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል ከህዳር 16 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለ16 ተከታታይ ቀናት እየተከበረ ይገኛል።

በዘመቻው እያንዳንዱ ቀናት የራሳቸው የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶላቸው የሚከበሩ ሲሆን፣ በእነዚህ ቀናት ወንዶች የፀረ ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ አጋር እንደሆኑ ለማሳየት ነጭ ሪባን ያስራሉ፣ ሴቶቹ ደግሞ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ሪባን ያስራሉ፡፡በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ጾታ የማይለይ ሁሉንም የሚመለከት ማኅበራዊ ችግር መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ይቁም የሚለው ዘመቻ መነሻ የተፈጸመው እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 6 ቀን 1989 በአገረ ካናዳ በሞንትሪያል ኩቤክ ከተማ በኢኮል ፓሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመ ግድያ ነው፡፡ ማርክ ሊፓይን የተባለ የ25 ዓመት ወጣት በዕለቱ 11 ሰዓት አካባቢ የሞንቲሪያል ዩኒቨርሲቲ አካል ወደሆነው የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ይገባል፡፡ ኮሌጁን በሚገባ የሚያውቀው ሊፓይን ወደ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል ያመራል፡፡ 50 ተማሪዎች ካሉበት በሁለተኛው ፎቅ ከሚገኘው አንዱ ክፍል ይገባና ሁሉም እንዲያዳምጡት ይጠይቃቸዋል፡፡ ተማሪዎቹም ንግግሩ የቀልድ መስሏቸው ቸል ሲሉት በቦርሳው የያዛትን ሽጉጥ በማውጣት ወደ ጣራው ይተኩሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም ተደናግጠው ለመሸሽ ሲሞክሩ ከተማሪዎቹ ውስጥ ወንዶቹና ሴቶቹ ተለይተው እንዲቆሙ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ከ50 ተማሪዎች ውስጥ ሴቶች ባንድ ጥግ ቀሪዎቹ ወንዶች ደግሞ በሌላው ጥግ ይቆማሉ፡፡ ሊፓይን ወንዶቹ ከክፍሉ እንዲወጡ ካዘዘ በኋላ ‹‹እዚህ ክፍል ለምን ሽጉጥ ይዤ እንዳመጣሁ የሚነግረኝ አለ?›› በሚል ይጠይቃቸዋል፡፡ ከሴቶቹ ተማሪዎች አንዷ ‹‹አናውቅም›› ስትል መልስ ትሰጣለች፡፡ እሱም ‹‹I am fighting feminism›› ሴቶች የወንዶቹን ያህል መብት ይኑራቸው የሚለውን ሐሳብ ለመታገል ነው፤›› ሲል ያምባርቅባቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተማሪዎቹ አንዷ ‹‹ተመልከተን! እኛ የምሕንድስና ተማሪዎች ነን፡፡ መደበኛ ሕይወት ለመኖር የምናስብ እንጂ ሴቶች ከወንዶች የተለየ መብት ያግኙ ብለን ለመጮህ የተዘጋጀን ፌሚኒስት አይደለንም፤›› በማለት በማስተዛዘን ትመልስለታለች፡፡ ማርክ ሊፓይንም ‹‹እናንተ ሁላችሁም ሴቶች ናችሁ፡፡ ነገ መሐንዲስ ትሆናላችሁ፡፡ በወንዶችም ላይ ጣታችሁን ትቀስራላችሁ፡፡ እኔ ፌሚኒስትን እጠላለሁ፤›› በማለት ከግራ ወደ ቀኝ በመደዳው ተማሪዎች ላይ ይተኩሳል፡፡ ስድስቱን ይገድላል፤ ሦስቱን ያቆስላል፡፡ ከዚያም በኮሪደሩ ላይ፣ ወደ ሌላ ክፍል፣ አንደኛ ፎቅ ወደሚገኘው የኮሌጅ ካፍቴሪያ፣ ወደ ሦስተኛ ፎቅ እየተዘዋወረና እየተኮሰ ሰውን መጉዳት ተያያዘው፡፡ ከ20 ደቂቃ የተኩስ ቆይታ በኋላ ሊፓይን ጭንቅላቱ ላይ ተኩሶ ራሱን አጠፋ፡፡ በዚህች አጭር ደቂቃ 14 ሴቶችን (12 የምሕንድስና ተማሪዎችን፣ አንድ የነርሲንግ ተማሪና አንድ የዩኒቨርሲቲውን ሴት ሠራተኛ) ገደለ፡፡ አራት ወንዶችን ጨምሮ ሌሎች አሥራ አራት ሰዎችን አቆሰለ፡፡

ከአደጋው በኋላ ሊፓይን  ራሱን ለማጥፋት ሲያስብ የጻፈው ደብዳቤና ለሌሎች ጓደኞቹ የጻፋቸው ሁለት ደብዳቤዎች በኪሱ ተገኝተዋል፡፡ ከደብዳቤዎቹ ይዘት ሊፓይን ፊሚኒስቶችን እንደሚጠላና ሊገደሉ ይገባል በሚል የአሥራ ዘጠኝ ታዋቂ ሴቶችን ስም ጽፏል፡፡ ሌፓይን ራሱ ምክንያታዊ እንደሆነ የሚገልጸው ይህ ደብዳቤ፣ ፌሚኒስቶች ሕይወቱን እንዳበላሹበት ይገልጻል፡፡ የሕይወት ታሪኩ እንደሚያሳየው ሊፓይን ከፈረንሳይ ተናጋሪ ካናዳዊ እናትና ከአልጀሪያዊ አባት የተወለደ ሲሆን፣ አባቱ ሴቶችን የሚንቅ፣ ሚስቱን የሚሳደብና የሚማታ፣ የእናትና የልጅን መልካም ግንኙነት የማይወድ ነበር፡፡ በሰባት ዓመቱ እናትና አባቱ የተለያዩ ሲሆን፣ ከእናቱ ጋር ሆኖ በቤተሰቦቿ አድጓል፡፡ ሊፓይን ጥሩ አዕምሮ የነበረው ግን ጭንቀት ያለበት ፌሚኒስቶትን የሚጠላ፣ ሙያ ያላቸውንና በተለይም ፖሊስነትን የመሰሉ ለወንድ መተው አለባቸው ብሎ የሚያስባቸውን ሥራዎች የሚሠሩ ሴቶችን የማይወድ እንደነበር ከሞቱ በኋላ የወጣ ሪፖርት ገልጿል፡፡

በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ማናቸውም ዓይነት መድሎን ለማስወገድ የተፈረመው ስምምነት (CEDAW) በአንቀጽ 1 በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት (Gender Based Violence) ሴቶች ሴት በመሆናቸው ብቻ የሚፈጸምባቸው ወይም በኅብረተሰቡ ሴቶችን በተለየ የሚመለከት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡ ጥቃቱ አካላዊ፣ አዕምሮአዊና ወሲባዊ ጥቃትን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ሴቶችን የማያስፈራራ፣ የሚያስገድድና ነፃነታቸውን የሚነፍግ ድርጊት ነው፡፡ በአገራችን ይህንን ትርጉም የሚያሟሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች መኖራቸው ለሁሉም ግልፅ  ነው፡፡ በሀገራችን ሴቶችን የመጨፍጨፍ ድርጊቶች ባናስተውልም የሚደበደቡ፣ በስለት የሚወጉ፣ አሲድ የሚደፋባቸው፣ በብዙ ወንዶች የሚደፈሩ፣ በቤት ውስጥ ጥቃት የሚደርስባቸው፣ የሚሰደቡ፣ የሚለከፉ ብዙ  ናቸው፡፡ እነዚህ የ16 ቀናት ንቅናቄ እነዚህ ድርጊቶች እንዲወገዱ ካልተቻለም እንዲቀንሱ ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ቀናቱም ካለፉ በኋላ በየዕለት ኑሮአችን ሴቶችን ከጥቃት የመንከባከብ ግዴታ በሁሉም ላይ ይጥላል፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

80 ሚሊዮን ሰዎች የሚታደሙበት ትዕይንት!

Next Post

ኢትዮጵያ እና ብራዚል በስኳር ኢንዱስትሪው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መከሩ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ኢትዮጵያ እና ብራዚል በስኳር ኢንዱስትሪው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መከሩ

ኢትዮጵያ እና ብራዚል በስኳር ኢንዱስትሪው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መከሩ

ቴክኖሎጂ አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር ያለው ሚና

ቴክኖሎጂ አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር ያለው ሚና

የተንሰራፋውን ሙስና ለመግታት የስራ እድል ፈጠራ ሊጠናክር ይገባል ተባለ

የተንሰራፋውን ሙስና ለመግታት የስራ እድል ፈጠራ ሊጠናክር ይገባል ተባለ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?