፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 12 2017| NBC ETHIOPIA-የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ዕዝ አወጣ፡፡
ከኔታንያሁ ባሻገር የቀድሞው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮዓቭ ጋላንት እና የሐማስ ጦር አዛዥ የእስር ትዕዛዝ ወቶባቸዋል።
የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICC) ዳኞች በእስራኤል የቀረበውን መከራከሪያ ውድቅ አድርገውታል።
ምንም እንኳን መሀመድ ዴኢፍ በእስራኤል ጦር ተገድለዋል ቢባልም የእስር ትዕዛዙ ወቶባቸዋል።
በጋዛው ጦርነት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ፥ሰብዓዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን ፈጸምዋል በሚል ነው ሶስቱም የእስር ትዕዛዙ የወጣባቸው።
በ-ቢንያም ካሴ












