በጋዛ ሠርጥ የሀማሱ መሪ ካሊል አል ሀያ በሰጡት ማብራሪያ በጋዛ ሠርጥ ያለው ጦረነት ካላበቃና የእስራኤል ጦር ሀይል ከምድሩ ካለወጣ በቀር ምንም አይነት የእስረኛ እና የታጋች ልውውጥ አይኖርም ነው ያለው።
አል ሀያ መገለጫውን የሰጡት ከአል አቅሣ የቴሌቪዢን ቻናል ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው አል ሀያ በማብራሪያቸው የእስራኤል ወረራ የማያበቃ ከሆነ ለምንድነው ሀማስ ታጋቾቹን የሚለቀው ሲሉም ነው የጠይቁት።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካው አምባሳደር በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ ሀገራቸው ድጋፏን የምትሰጠው የእስራኤል ታጋቾች የሚቀቁ ከሆነ በቻ ነው ሲሉ በአፅንዖት ገልጸዋል ዘገባው የኤዢያ ዋን ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ












