፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 12 2017| NBC ETHIOPIA-ዩክሬን የምዕራባዊያኑን የጦር መሣሪያ ተጠቅማ የሩሲያን ውስጠኛ ክፍል መምታቷን ተከትሎ ሩሲያ የበቀል ርምጃዋን በአዲሱ ሚሳኤል የዩክሬኗን ዋና ከተማ ኪቪን ለመምታት መዛቷ ነው የተሰማው ፡፡
የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ባሰራጩት ዘገባቸው የቭላዲሚር ፑቲን የጦር ሀይል አዲስ የተሰራውን የአር-ኤስ-26 አህጉር አቋራጭ ሚሳይል በኪቪ ከተማ ላይ ለመተኮስ ተዘጋጅቷል ነው የተባለው፡፡
ምዕራባውያኑ መንግስታት በበኩላቸው ከሩሲያ ወገን ከባድ የአየር ጥቃት ያሰጋል ሲሉ አሜሪካ ጨምሮ ጣሊያን ግሪክ ስፔን በኪቪ ያለውን ኢምባሲዎቻቸውን መዝጋታቸው ታውቋል፡፡
ዩክሬን ረብዕ አመሻሽ ላይ እንግሊዙን የስቶርም ሻዶው ክሩይዝ ሚሳኤል በሩሲያ ኩርስክ ግዛት የዕዝ ማዕከል ላይ መተኮሷና ጥቃት መፈፀሟን የኒው አየርላንድ ሄራልድ ዘገባ ያስረዳል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት












