፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 11 2017| NBC ETHIOPIA-የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት፣ በጥራትና በውጤታማነት እንዲፈፅሙ የሚያስችል መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሔደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞችን አዋጅ ለማሻሻል የቀረበውን ረቂት አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በአዋጁ አላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የአዋጁ መሻሻል ለተገልጋዮች የተሳለጠና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት፣ ቀልጣፋና የዘመነ የአሰራር ስርአት ለመዘርጋት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሲቪል ሰርቪሱ ለሀገር እድገት የላቀ ሚናውን እንዲወጣና በመንግስት ሰራተኞች መካከል ጤናማ የሆነ ውድድር ለመፍጠርም ያለመ ነው ብለዋል።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተልዕኳቸውን በብቃት፣ በጥራትና በውጤታማነት እንዲፈፅሙ አዋጁ መልካም እድል የሚፈጥር መሆኑንም አስረድተዋል።
የሰው ሃብት ምልመላና ቅጥር ክህሎት፣ እውቀትና ብቃትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን የሚያደርግ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
የምክር ቤት አባላትም አዋጁ ለቀልጣፋ አገልገሎት አሰጣጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ተጨማሪ ማብራሪያ ያሻቸዋል ያሏቸውን ጥያቄዎችም አንስተዋል።
የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፤ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የምክር ቤቱም የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል ዘገባው የኢዜአ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












