፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 10 2017| NBC ETHIOPIA – የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
የምክር ቤቱ አባል ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን የተነሣው በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።
ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልከት አባሉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።












