፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 09 2017| NBC ETHIOPIA-በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በዛሬው ዕለት መስጠት ተጀመረ፡፡
እድሜያቸው ከዘጠኝ እስከ አስራ አራት አመት ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ዛሬ በትምህርት ቤት እና ቤት ለቤት መስጠት ተጀምሯል፡፡

በክትባት ማስጀመር ፕሮግራሙ ላይ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሃይለኢየሱስ ሰለሞን፣ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ሞሚና አሊ፣ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ በረከት ገደፋው እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
ክትባቱ ከዛሬ እስከ ህዳር 13/2017 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን ወላጆች ልጆቻቸው የማህፀን በር ካንሰር ክትባቱን እንዲወስዱ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ መልዕክት ማስተላለፉን አማራ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት












