፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 06 2017| NBC ETHIOPIA- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ተወያይተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት የዓለም ባንክ በከተማ አስተዳደራችን በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ፣ በአቅም ግንባታ፣ በተማሪዎች ምገባ፣ በትራንስፖርትና መንገድ ዘርፍ እንዲሁም በውሃና ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተሰራ ያለውን ስራ ከጐበኙ በኋላ ይበልጥ ለመደገፍ የሚያስችል ውይይት አካሂደናል ብለዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












