፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 20 2017| NBC ETHIOPIA-በስፔን ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ቢያንስ የ62 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
በደቡባዊ ምስራቅ ስፔን የዘነበው ከባድ ዝናብ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ጎርፍ ከማስከተሉም ባሻገር ከ1መቶ ሺህ በላይ ሰዎችን ከኃይል አግልግሎት ውጭ አድርጓል ፡፡
በቫሌንሺያ ግዛት አቅራቢያ ቺቫ በተሰኘ ቦታ ላይ ለስምንት ሰዓታት የዘለቀው ዝናብ አደገኛ በመሆኑ የተጎጂዎችን ቁጥር ለመግለጽ ከባድ ሆኗል ፡፡
መላው ስፔን በከባድ ዝናብ እየተናወጠ ሲሆን ጎርፉን ለመቆጣጠርም አደገኛ ሆኗል ተብሏል ፡፡
የስፔኑ የቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ህዝባቸውን አንተዋችሁም በሚል አጽናንተዋል ሲል የዘገበው ዘ ዋሽንግተን ፖስት፡፡
በ-ቢንያም ካሴ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook – https://www.facebook.com/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












