Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ተመድ ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች እድገት እና ዘላቂ ልማትን ለማሳካት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

November 1, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ጥቅምት 20 2017| NBC ETHIOPIA-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች እድገት እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የጀመረችውን ጉዞ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቆ ኢትዮጵያ የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ እየተገበረች ያለውን የበጀት መርሃ ግብርም አድንቋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው በተመድ የሴቶችን ጉዳይ የሚከታተለው ዩኤን ውመን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኒያራድዛይ ጉምቦንዝቫንዳ ጋር ተወያይተዋል።ውይይቱ ኢትዮጵያ በስርዓተ ጾታ ፋይናንስ፣ የስርዓተ ጾታ እኩልነት ለማረጋገጥ እና ሴቶችን ለማብቃት እያደረገች የምትገኛቸው ጥረቶች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች የሴት መራሮችን ሚና ለማሳደግ፣ ሁሉን አቀፍ እድገት እውን ለማድረግ እና በሁሉም ደረጃዎች የሚሰጡ ውሳኔዎች አሳታፊ እንዲሆኑ አበክራ እየሰራች ነው ብለዋል።

ከዚህ አንጻር ዩኤን ውመን የኢትዮጵያ የስርዓተ ጾታ እኩልነት መከታተያ ስርዓት ለማሻሻል፣ የሴቶችን የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት እና የሴቶች የፋይናንስ አካታችነት እና ተደራሽነት ለማረጋጋጥ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድጋፎቹ በፋይናንስ አቅርቦት እና ተደራሽነት ያሉ ውስንነቶችን ለመፍታት አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ስርዓተ ጾታን ያማከለ የበጀት ዝግጅት፣ የስርዓተ ጾታ የበጀት መግለጫ እና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ያሳየችው መሻሻል በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

ዩኤን ውመን በኢትዮጵያ ዘላቂ የስርዓተ ጾታ ፋይናንስ ስርዓት ለመዘርጋት እና ሴቶችን በማብቃት ዘላቂነት ያለው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለማምጣት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን መደገፉን እንዲቀጥል ሚኒስትር ዴኤታዋ ጥሪ አቅርበዋል።

የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በፌደራል እና በክልል ደረጃ የአቅም ግንባታ ስራ የማከናወን አስፈላጊነት አንስተዋል።

የዩኤን ውመን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኒያራድዛይ ጉምቦንዝቫንዳ ኢትዮጵያ የስርዓተ ጾታ እኩለነትን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን በመተግበር እየወሰደች ያለውን እርምጃ አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ የስርዓተ ጾታ እኩልነትን የሚያሻሽሉ ጠንካራ እና የሚደነቁ የበጀት ኢኒሼቲቮችን እየተገበረች እንደምትገኝ እና ይህም በቀጣናው ላሉ ሌሎች አገራት ምሳሌ መሆን የሚችል ነው ብለዋል።

ዩኤን ውመን ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች እድገት እና ዘላቂ ልማትን የጀመረችውን ጉዞ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሴሲል ሙካሩቡጋ ዩኤን ውመን ኢትዮጵያ ስርዓተ ጾታን ያማከለ የበጀት ዝግጅቷን እንድታሻሻል እና ሁሉን አካታች እድገት እንድታስመዘግብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

📌 YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

📌TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

📌 Website – https://nbcethiopia.com/news/

📌 Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBCEthiopia

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

ጤና ሚኒስቴር ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ ለተጠሪ ተቋማት 260 ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ አደረገ

Next Post

የስፔን ዶፍ ዝናብና ጎርፍ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የስፔን ዶፍ ዝናብና ጎርፍ

የስፔን ዶፍ ዝናብና ጎርፍ

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን የተሳታፊ ምርጫ አካሄደ

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን የተሳታፊ ምርጫ አካሄደ

አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ መስራት አለባቸው -ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)

አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ መስራት አለባቸው -ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?