፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 20 2017| NBC ETHIOPIA-ሶስተኛ ቀኑ በያዘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃግብር የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን መርጠዋል።
እያንዳንዱ የማህበረስብ ክፍል 8 ሰዎች በመምረጥ በአጠቃላይ 80 የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች መመረጥ ችለዋል።
በሂደቱ በ10ሩም የማህበረሰብ ክፍሎች ሴቶችን ተሳታፊነት ለማድረግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥረት አድርጓል።

ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሲነሱበት የቆየው የሶስት ቀኑ የአጀንዳ ማቅረብና ተሳታፊ መረጣ በማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች ዘንድ ተጠናቋል።
በቀጣይ ቀናት ሌሎች ባለድርሻ አካላት አጀንዳ የማቅረብ እና ተሳታፊ የመምረጥ ሂደት በተመሳሳይ መልኩ ያከናውናሉ።
በዚህ መሰረት መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚወክሉ ተወካዮች፣ ከሶስቱ የመንግስት አካላት የተውጣጡ የተቋማት ተወካዮችና የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Facebook – https://www.facebook.com/












