፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 08 2017| NBC ETHIOPIA-አራተኛው የብሪክስ ዋና እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ በሩሲያ ካዛን እየተካሄደ ነው።
በወቅቱ ሊቀመንበር ሩሲያ እየተመራ ባለው ስብሰባ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉዳይ ምክትል አስተባባሪ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በመሳትፍ ላይ ይገኛል።

በዚህ ስብሰባ ዋና አስተባባሪዎች እና ምክትል አስተባባሪዎች የካዛን ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት እና የብሪክስ አጋር አገራት አሠራር ማዘጋጀት ላይ አተኩረው እንደሚሰሩ ተገልጿል።

16ኛውየብሪክስ አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ ከጥቅምት 12 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. በሩሲያ ካዛን ከተማ እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።












