፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 23 2017| NBC ETHIOPIA-በአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ቅዳሜ ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የጽዳት ዘመቻ ተከናወነ።
በመርሃግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ሌሎች የመንግስት ስራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ ሃደ-ሲንቄዎች፣ ቄሮዎች፣ ቀሬዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት የጽዳት መርሐ ግብሩ የአንድነት፣ወንድማማችነትና እህትማማችነት ባህል የሚጠናከርበትና የሚቀጥል መድረክ ነው።
ኢሬቻ ለአንድነትና ለሀገር ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ በመሆኑ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
በዓሉ በአዲስ አበባ መከበሩ የቱሪዝም ፍሰትን ማሳደጉንና ለከተማዋ ድምቀት መፍጠሩን አንስተዋል።
በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቅበትን ዝግጅት ማድረጉን ገልፀው፤ የማክበሪያ ስፍራው ጽዱና ምቹ ተደርጓል ብለዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሙባሪክ ከማል በበኩላቸው፤ ኢሬቻ የአንድነት፣ የሰላምና የፍቅር በዓል መሆኑን ገልጸዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማም በዓሉ ደምቆ እንዲከበር አካባቢውን የማስዋብ ሥራ መስራቱን ገልፀዋል።
በቀጣይም እንግዶችን በመልካም መስተንግዶ ለመቀበልና ለመሸኘት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












