፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 20 2017| NBC ETHIOPIA-በአፋር ክልል ከነገ ጀምሮ የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ይካሄዳል ተብሏል፡፡ በክልሉ የሚደረገው የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ከመስከረም 21 እስከ 27 የሚቆይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አይሮሪት መሐመድ(ዶ/ር) በአፋር የአጀንዳ ማሰባሰቡን ሂደት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
ኮሚሽነሯ በመግለጫቸው በክልሉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ባሉበት ከነገ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ይካሄዳል ብለዋል።
በመድረኩ ከ49 ወረዳዎች የተመረጡ ከ800 በላይ የህብረተሰብ ተወካዮች እንዲሁም ከ700 በላይ የሚሆኑ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት መሆኑንም አንስተዋል ።
በመግለጫቸው እንደጠቀሱት ይህ የምክክር መድረክ የህብረተሰብ ተወካዮች ለሀገራዊ መግባባት ይበጃሉ ያሏቸውን ሐሳቦችና መሠረታዊ ሐገራዊ ጉዳዮችን በአጀንዳነት አንስተው በህዝባዊ ውይይቱ የሚዳብርበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለተከታታይ ስድስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ሀገራዊ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ሀገራዊና ክልላዊ ፋይዳውን በመረዳት ከህብረተሰቡ የተወከሉት ተሳታፊዎች በንቃት መሳተፍ እንደሚገባቸው አፅንኦት ተሰጥቷል፡፡
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












