፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 21 2017| NBC ETHIOPIA- በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ በ2016/17 የምርት ዘመን ከሩዝ ሰብል ከ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።
የፎገራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ውለታው ተረፈ እንደተናገሩት፤ ምርታማነትን ከፍ ለማድረግ የተፈጥሮ ማዳበሪያን መጠቀም የተሻለ ምርት እምደሚያስኝ ገልጸው በምርት ዘመኑ በሩዝ ከተሸፈነው 34 ሺ 822 ሄክታር መሬት 1 ሚሊዮን 918 ሺ 510 ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል ብለዋል።

በወረዳው ሩዝና በቆሎ በብዛት እየለማ እንደሚገኝ አክለው የገለፁት ሃላፊው፤ በ401 ክላስተር 28 ሺ 991 ሄክታር መሬት በበሩዝ ኮሞዲቲ ክላስተር የተሸፈነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በ2016/17 የምርት ዘመን በ28 ቀበሌዎች የሚገኙ የትምህርት ቤት፣ የገበሬ ማሰልጠኛ ተቋማትን፣ የቤተ ክርስቲያን እና የወል መሬቶችን ትኩረት ተሰጥቶ ወደ ምርት እንዲገቡ በማድረግ ተጨማሪ ምርት ለማግኘት ሰፊ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ከአማራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












