፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 18 2017| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአፋር ክልል ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ማከናወን ይጀምራል፡፡
ኮሚሽኑ በሂደቱ በክልሉ ከሚገኙ 49 ወረዳዎች የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍል ወኪሎችን፣ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ማህበራት ወኪሎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና ከክልሉ የመንግስት አካላት የተወከሉ ተወካዮችን ያሳትፋል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በይፋ የተጀመረው የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ እስከአሁን በ5 ክልሎች እና በ2 የከተማ አስተዳድሮች ሲከናወን ቆይቷል፡፡
በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሲዳማ ክልል እና የሐረሪ ክልል ኮሚሽኑ አጀንዳን ያሰባሰበባቸው የሀገራችን አካባቢዎች ናቸው፡፡
ኮሚሽኑ በቀጣዩቹ ጊዜያት በሶማሌ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እና በኦሮሚያ ክልሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍን ለማከናወን ዝግጅቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












