፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 15 2017| NBC ETHIOPIA-የቻይና ጦር ሀይል ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የአህጉር አቆራጭ የባለስቲክ ሚሳይል ሙከራ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የአህጉር አቋራች የባለስቲክ ሚሳይል ሙከራ በተሳካ ሁኔታ ማወንጨፏን በይፋ የገለጸችው ዛሬ ማለዳ ላይ ነው፡፡
የቻይና ህዝቦች ነፃነት ጦር ሀይል የባለስቲክ ሚሳይል ሙከራውን ያደገረው ወደ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሆኑም ነው የተገለፀው፡፡የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሁኑ የሚሳይል ሙከራ ከተያዘው አመታዊ ዕቅድ አንዱና ከባዱ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡
ቻይና በዚህ ወቅት ከአምስት በቶ በላይ የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳላትና ከዚያ ውስት ደግሞ ሶስት መቶ ሃምሳው የአህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳይሎች እንበደሆኑ እንዲሁም በአውሮፓውያኑ 2030 ቻይና ከአንዲ ሺ በላይ የኑክሌር ጦር መሳሪ እንደሚኖሩተረ የአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን በ2030 ያወጣው ሪፖርት ያሳያል ዘገባው የስትሬት ታይምስ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












